Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጥበበኞች ያድምጡ፤ ትምህርታቸውንም ያዳብሩ፤ አስተዋዮችም መመሪያ ያግኙበት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጠቢብ እነዚህን በመስማት ዐዋቂነትን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነዚህ ምሳሌዎች ጠቢባን ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ፥ አስተዋዮችም ተጨማሪ መመሪያ የሚሆናቸውን ምክር እንዲያገኙ ያደርጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 1:5
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው።


ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።


ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ደ​ሚ​ነ​ገር እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ው​ንም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


ያለ​ዚያ ግን ተመ​ከር፥ ይህ​ንም ስማ፤ የን​ግ​ግ​ሬ​ንም ቃል አድ​ምጥ።


“ሰለ​ዚህ እና​ንተ አእ​ምሮ ያላ​ቸሁ ሰዎች ስሙኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ትበ​ድሉ ዘንድ አት​ው​ደዱ። ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም ጻድ​ቁን አታ​ው​ኩት።


የልብ ጥበ​በ​ኞች እን​ዲህ ይላ​ሉና፦ ጠቢብ ሰው ነገ​ሬን ይሰ​ማ​ኛል።


እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ንጉሡ አሜ​ስ​ያስ፥ “በውኑ የን​ጉሡ አማ​ካሪ ልት​ሆን ሹሜ​ሃ​ለ​ሁን? ቅጣት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። ነቢ​ዩም፥ “ይህን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ምክ​ሬ​ንም አል​ሰ​ማ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋህ እን​ዳ​ሰበ አወ​ቅሁ” ብሎ ዝም አለ።


በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


ጠብ​ቁት፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ ይህን ሥር​ዐት ሁሉ ሰም​ተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢ​ብና አስ​ተ​ዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአ​ሕ​ዛብ ፊት ጥበ​ባ​ች​ሁና ማስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ ይህ ነውና፤


“እና​ንተ ጥበ​በ​ኞች፥ ቃሌን ስሙ፤ እና​ን​ተም ዐዋ​ቂ​ዎች፥ መል​ካም ነገ​ርን አድ​ምጡ።


ጥበብን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸልም አትበሉት።


ሰነፎችን አትገሥጽ እንዳይጠሉህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።


የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥ የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።


ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል።


ክፉ ሰው ሲዋረድ የዋህ ሰው ዐዋቂ ይሆናል፤ ጥበብን የሚረዳ ሰውም ዕውቀትን ይቀበላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች