Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ፊልጵስዩስ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ፍጹ​ም​ነ​ታ​ች​ሁም በሰው ሁሉ ዘንድ ይታ​ወቅ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅርብ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ገርነታችሁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ጌታ ቅርብ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ መምጫው ቀርቦአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ደግነታችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ጌታ ተመልሶ ሊመጣ ቀርቦአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ፊልጵስዩስ 4:5
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?


“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን የማ​ይ​ወ​ደው የተ​ለየ ይሁን፤ ጌታ​ችን ይመ​ጣል።


እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም?


ነገር ግን በመ​ብል ምክ​ን​ያት ወን​ድሜ የሚ​ሰ​ና​ከል ከሆነ ወን​ድ​ሜን እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥጋን አል​በ​ላም።


የሚ​ታ​ገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታ​ገ​ሣል፤ እነ​ር​ሱስ የሚ​ጠ​ፋ​ው​ንና የሚ​ያ​ል​ፈ​ውን የም​ስ​ጋ​ና​ቸ​ውን ዋጋ አክ​ሊል ያገኙ ዘንድ ይበ​ረ​ታሉ፤ እኛ ግን የማ​ያ​ል​ፈ​ውን አክ​ሊል ለማ​ግ​ኘት እን​ታ​ገ​ሣ​ለን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።


ሌሎች ልማድ አድ​ር​ገው እንደ ያዙት ማኅ​በ​ራ​ች​ንን አን​ተው፤ እርስ በር​ሳ​ችን እን​መ​ካ​ከር እንጂ፤ ይል​ቁ​ንም ቀኑ ሲቀ​ርብ እያ​ያ​ችሁ አብ​ል​ጣ​ችሁ ይህን አድ​ርጉ።


“ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ፈጥኖ ይደ​ር​ሳል፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።


በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።


ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፤


ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ!ጅ ና።


እነሆም “በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፤” አለኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች