Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በዚ​ያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። እነ​ዚ​ያም ሰዎች “እኛ በሰ​ው​ነ​ታ​ችን ርኵ​ሰት ያለ​ብን ሰዎች ነን፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በጊ​ዜው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ና​ቀ​ርብ ስለ ምን እን​ከ​ለ​ከ​ላ​ለን?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሙሴን፣ “በሬሳ ምክንያት ረክሰናል፤ ታዲያ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነን በተወሰነው ጊዜ እንዳናቀርብ ለምን እንከለከላለን?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነዚያም ሰዎች እርሱን እንዲህ አሉት፦ “የሞተውን ሰው ሬሳ በመነንካት ብንረክስም እንኳ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የጌታን ቁርባን በተወሰነለት ጊዜ እንዳናቀርብ ለምን እንከለከላለን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “እኛ በድን በመንካታችን ረክሰናል፤ ነገር ግን ከቀሩት እስራኤላውያን ተለይተን በወቅቱ ለእግዚአብሔር መባ እንዳናቀርብ ስለምን እንከለከላለን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነዚያም ሰዎች፦ በሞተ ሰው ሬሳ ረክሰናል፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን? አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:7
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

‘ይህ በግ​ብፅ ሀገር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንን የአ​ዳነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት ነው’ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሕዝ​ቡም ተጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በጊ​ዜው ፋሲ​ካ​ውን ያድ​ርጉ።


በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ርኵ​ሰት የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ሰዎች መጡ፤ ስለ​ዚ​ህም በዚያ ቀን ፋሲ​ካን ያደ​ርጉ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ የሚ​ያ​ዝ​ዘ​ውን እስ​ክ​ሰማ ቈዩ” አላ​ቸው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ከበ​ግና ከላም መንጋ ሠዋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች