Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ አዘዘ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዛሉ፤ እነርሱም በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በጌታ ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በጌታም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ የጌታን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ድንኳናቸውን የሚተክሉትም ሆነ ሰፈር ለቀው ወደ ፊት የሚጓዙት እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:23
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ​ንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቃ​ች​ኋል።


ደመ​ና​ውም በድ​ን​ኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተ​ቀ​መጠ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።


የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”


አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፥ ደስ ይለ​ኛል፥ ሰቂ​ማ​ንም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥ የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።


ወደ ሸለቆ እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ ከብ​ቶች፥ እን​ዲሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ወደ ዕረ​ፍት አመ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ሁም ለራ​ስህ የከ​በረ ስምን ታደ​ርግ ዘንድ ሕዝ​ብ​ህን መራህ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እን​ዳ​ዘዘ ተጓዙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች