Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አን​ዳ​ንድ ጊዜም ደመ​ናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀ​መጥ ነበር፤ በጥ​ዋ​ትም ደመ​ናው በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም ቢሆን ደመ​ናው በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደመናው ከምሽት እስከ ንጋት ብቻ ይቈያል፤ ደመናው ንጋት ላይ ሲነሣም ጕዟቸውን ይጀምራሉ፤ ቀንም ይሁን ሌሊት ደመናው ከተነሣ ጕዞ ይጀምራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቈይ ነበር፤ በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዛሉ፥ ወይም ባለማቋረጥ ቀኑንም ሌሊቱንም የሚቈይ ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አንዳንድ ጊዜ ደመናው የሚቈየው ከምሽት እስከ ንጋት ብቻ ነበር፤ ስለዚህ ደመናው እንደ ተነሣ ወዲያውኑ ጒዞ ይቀጥላሉ፤ ወይም ደመናው ቀንና ማታ ቢቈይ ደመናው ሲነሣ ይሄዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀመጥ ነበር፤ በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር፤ በቀንም በሌሊትም ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:21
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ታበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ቀን በደ​መና ዐምድ፥ ሌሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ መራ​ሃ​ቸው።


አንተ ግን ምሕ​ረ​ትህ ብዙ ነውና በም​ድረ በዳ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም፤ በመ​ን​ገ​ድም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የደ​መና ዓም​ድን በቀን፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዓም​ድን በሌ​ሊት ከእ​ነ​ርሱ አላ​ራ​ቅ​ህም።


ደመ​ናው ድን​ኳ​ኑን በጋ​ረ​ደ​በት ቀን ቍጥር ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይሰ​ፍሩ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር።


ደመ​ና​ውም እስከ ወር ቈይቶ በድ​ን​ኳኑ ላይ ቢቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ፈ​ራ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር፤ ነገር ግን በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች