Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ድን​ኳ​ን​ዋን በተ​ከ​ሉ​በት ቀን ደመ​ናው የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሸፈ​ናት፤ ከማ​ታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በድ​ን​ኳኑ ላይ እንደ እሳት ይመ​ስል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማደሪያው በተተከለ ዕለት ደመናው የምስክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ከምሽት እስከ ንጋት ድረስ ማደሪያውን የሸፈነው ደመና እሳት ይመስል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ማደሪያውም በተተከለ ቀን ደመናው ማደሪያውን፥ የምስክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ከማታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በማደሪያው ላይ ነበረ፤ እርሱም እንደ እሳት ያለ አምሳል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የመገናኛው ድንኳን በተተከለበት ቀን ደመናው ድንኳኑን ሸፈነው፤ ከማታ ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በድንኳኑ ላይ እንደ እሳት ያበራ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ማደሪያውም በተተከለ ቀን ደመናው የምስክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ከማታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በማደሪያው ላይ እንደ እሳት ይመስል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:15
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ታበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ቀን በደ​መና ዐምድ፥ ሌሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ መራ​ሃ​ቸው።


አንተ ግን ምሕ​ረ​ትህ ብዙ ነውና በም​ድረ በዳ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም፤ በመ​ን​ገ​ድም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የደ​መና ዓም​ድን በቀን፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዓም​ድን በሌ​ሊት ከእ​ነ​ርሱ አላ​ራ​ቅ​ህም።


በሥ​ራ​ቸ​ውም ረከ​ሰች፥ በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውም አመ​ነ​ዘሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገድ ሊያ​ሳ​ያ​ቸው ቀን በዐ​ምደ ደመና፥ ሌሊ​ትም በዐ​ምደ እሳት ይመ​ራ​ቸው ነበር።


ዐምደ ደመ​ናው በቀን፥ ዐምደ እሳ​ቱም በሌ​ሊት ከሕ​ዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላ​ለም።


ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በፊ​ተ​ኛው ቀን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ትተ​ክ​ላ​ለህ።


ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች።


ደመ​ና​ውም በላዩ ስለ​ነ​በር ድን​ኳ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገባ ዘንድ አል​ቻ​ለም።


ደመና በቀን በድ​ን​ኳኑ ላይ ነበ​ርና፥ እሳ​ቱም በሚ​ጓ​ዙ​በት ሁሉ በሌ​ሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በእ​ር​ስዋ ላይ ነበ​ርና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ጣል፤ በጽ​ዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌ​ሊ​ትም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል የእ​ሳት ብር​ሃን ይጋ​ር​ዳል፤ በክ​ብ​ርም ሁሉ ላይ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል።


ሙሴም ታቦቷ በተ​ጓ​ዘች ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ተነሣ፤ ጠላ​ቶ​ችህ ይበ​ተኑ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ህም ከፊ​ትህ ይሽሹ” ይል ነበር።


የዚ​ያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝ​ብህ መካ​ከል እንደ ሆንህ ሰም​ተ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐ​ይን እን​ደ​ሚ​ተ​ያይ ተገ​ል​ጠ​ህ​ላ​ቸ​ዋል። ደመ​ና​ህም በላ​ያ​ቸው ቆመች። በቀ​ንም በደ​መና ዐምድ ፥ በሌ​ሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ በፊ​ታ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።


ሙሴም በት​ሮ​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረ​ዳ​ቸው ሁሉም በባ​ሕር መካ​ከል አል​ፈው እንደ ሄዱ ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።


እር​ሱም ስፍ​ራን እን​ዲ​መ​ር​ጥ​ላ​ችሁ፥ ትሄ​ዱ​በ​ትም ዘንድ የሚ​ገ​ባ​ውን መን​ገድ እን​ዲ​ያ​ሳ​ያ​ችሁ ሌሊት በእ​ሳት፥ ቀን በደ​መና በፊ​ታ​ችሁ በመ​ን​ገድ ሲሄድ የነ​በ​ረ​ውን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች