Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ወይም ከት​ው​ል​ዶ​ቻ​ችሁ ዘንድ ማን​ኛ​ውም ሰው በሰ​ው​ነቱ ቢረ​ክስ፥ ወይም ሩቅ መን​ገድ ቢሄድ፥ ወይም በተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​በት ሀገር ያለም ቢሆን እርሱ ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን ያድ​ርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ከእናንተ ወይም ከዘሮቻችሁ ማንኛውም ሰው በሬሳ ምክንያት ቢረክስ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ማክበር ይችላል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው ሬሳን በመንካት ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ እንዲህም ሆኖ እንኳ ለጌታ የፋሲካን በዓል ያክብር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእናንተም ሆነ ከዘራችሁ ሰዎች በድን በመንካት ቢረክሱ ወይም ወደ ሩቅ አገር ለመሄድ በጒዞ ላይ ቢሆኑና የፋሲካን በዓል ለማክበር ቢፈልጉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:10
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የቂ​ጣ​ውን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብዙ ሕዝብ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እጅ​ግም ታላቅ ጉባኤ ነበረ።


እንደ ትእ​ዛ​ዙም ሳይ​ሆን ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ፥ ከይ​ሳ​ኮ​ርና ከዛ​ብ​ሎ​ንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይ​ነጹ ፋሲ​ካ​ውን በሉ።


ንጉ​ሡና አለ​ቆቹ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ፋሲ​ካ​ውን ያደ​ርጉ ዘንድ ተማ​ከሩ።


በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድ​ር​ጉት፤ ከቂጣ እን​ጀ​ራና ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፤አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፤በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።


የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከበ​ዓሉ አስ​ቀ​ድሞ ራሳ​ቸ​ውን ያነጹ ዘንድ ከየ​ሀ​ገሩ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ነበር።


አሁ​ንም ሰው ራሱን መር​ም​ሮና አን​ጽቶ ከዚህ ኅብ​ስት ይብላ፤ ከዚ​ህም ጽዋ ይጠጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች