Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከላ​ሞች አንድ ወይ​ፈን፥ ለእ​ህ​ሉም ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄ​ትን ይው​ሰዱ፤ ሌላ​ው​ንም የአ​ንድ ዓመት ወይ​ፈን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ይው​ሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በዘይት ከተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን ጋራ አንድ ወይፈን ይውሰዱ፤ ከዚያም ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆን ሌላ ወይፈን አንተ ትወስዳለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወይፈንን፥ ለእህሉም ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ቀጥሎም አንድ ወይፈንና ለእህል ቊርባን የተመደበውን በዘይት የተለወሰ ዱቄት ይውሰዱ፤ አንተም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርብ አንድ ወይፈን ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ወይፈንን፥ ለእህሉም ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 8:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


በአ​ንድ መሶ​ብም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑና ከሁ​ለቱ አውራ በጎች ጋር በመ​ሶብ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


እን​ዲሁ አሮን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች ወይ​ፈን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይግባ።


“ማና​ቸ​ውም ሰው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ቢያ​ቀ​ርብ፥ ቍር​ባኑ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይ​ትም ያፈ​ስ​ስ​በ​ታል፤ ነጭ ዕጣ​ንም ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ይህም መሥ​ዋ​ዕት ነው።


ከዚ​ህም በኋላ፥ የሠ​ሩት ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቃ​ቸ​ውና ንስሓ ቢገቡ ማኅ​በሩ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንን ያቀ​ር​ባሉ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ፊት ያመ​ጡ​ታል።


የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል።


“አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን፥ ልብ​ሱ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን፥ ሁለ​ቱ​ንም አውራ በጎች፥ የቂ​ጣ​ው​ንም እን​ጀራ መሶብ ውሰድ፤


ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች