Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 8:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ወን​ድ​ሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ል​ግል፤ ሰሞ​ና​ቸ​ው​ንም ይጠ​ብቅ። ነገር ግን አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ይተው። እን​ዲሁ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው በመገናኛው ድንኳን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያግዟቸዋል እንጂ ራሳቸው መሥራት የለባቸውም። ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምታሰማራቸው በዚህ መልኩ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የተሰጣቸውን ይጠብቁ ዘንድ ወንድሞቻቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለግላሉ፤ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩም። እንዲሁ ስለ ሥራቸው በሌዋውያን ላይ ታደርጋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 8:26
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ዕዳ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስ​ፈሩ፤ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ።”


ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፤ ይህንም አዘውትር።


ነገር ግን በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም በሮች በረ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም ውስጥ ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ይሠ​ዋሉ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ በፊ​ታ​ቸው ይቆ​ማሉ።


የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥር​ዐት፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የአ​ሮ​ንን ልጆች ሥር​ዐት ለመ​ጠ​በቅ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ድርሻ እኩ​ሌታ፥ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከእ​ን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ ከአ​ምሳ አንድ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ለሌ​ዋ​ው​ያን ትሰ​ጣ​ለህ።”


ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ለድ​ን​ኳ​ኑም አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ፤ ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ወደ አንተ አይ​ቅ​ረብ።


የሌ​ዋ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች አለቃ የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮ​ችን ይጠ​ብቅ ዘንድ የተ​ሾ​መው የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር ነው።


ከአ​ምሳ ዓመት በኋላ ከሥ​ራው ይሰ​ና​በት። ከዚ​ያም ወዲያ እርሱ አያ​ገ​ል​ግል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች