Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ፊት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ዘንድ ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር ሆነው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት ለማከናወን ገቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አስፈላጊውን በሌዋውያኑ አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ገቡ፤ ጌታ ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ለሙሴ ስለ ሌዋውያን በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሕዝቡ ሁሉን ነገር አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት ሌዋውያን በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ዝግጁዎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 8:22
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተነ​ሥ​ተው ሕዝ​ቡን ባረኩ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም ተሰማ፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ውም ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያው ወደ ሰማይ ዐረገ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘዘ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ነገር ግን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በዕ​ቃ​ዎ​ችዋ ሁሉ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋ​ው​ያ​ንን አቁ​ማ​ቸው። ድን​ኳ​ን​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​አ​ትም፤ በድ​ን​ኳ​ን​ዋም ዙሪያ ይስ​ፈሩ።


“ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ፤ ታነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ ስጦ​ታም አድ​ር​ገህ በፊቴ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሌዋ​ው​ያ​ንም ከኀ​ጢ​አት ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ፤ አሮ​ንም ስጦታ አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ አሮ​ንም ያነ​ጻ​ቸው ዘንድ አስ​ተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች