Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ስጦታ አድ​ር​ገህ አቅ​ር​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፤ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህም ለእግዚአብሔር አቅርባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሌዋውያንንም በአሮንና በልጆቹ ፊት ታቆማቸዋለህ፥ በጌታም ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ታቀርባቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ሌዋውያንን ለእኔ የተለየ ስጦታ አድርገህ ቀድስልኝ፤ አሮንንና ልጆቹንም በእነርሱ ላይ ሹማቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሌዋውያንንም በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ስጦታ አድርገህ አቅርባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 8:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሌዋ​ው​ያ​ንም ከኀ​ጢ​አት ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ፤ አሮ​ንም ስጦታ አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ አሮ​ንም ያነ​ጻ​ቸው ዘንድ አስ​ተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው።


አሮ​ንም ሌዋ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ስጦታ አድ​ርጎ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​ያ​ቸ​ዋል።


በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ውና ቅዱስ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ርቡ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርኅ​ራኄ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ይህም በዕ​ው​ቀት የሚ​ሆን አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ነው።


እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጡ ስጦ​ታ​ዎች ናቸው።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም በወ​ይ​ፈ​ኖቹ ራሶች ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጫኑ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረያ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርብ።


እን​ዲሁ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ፤ እነ​ር​ሱም ለእኔ ይሁኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች