Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 7:87 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

87 የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ ከእ​ህሉ ቍር​ባን ጋር ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዐሥራ ሁለ​ትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለ​ትም የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ፤ የኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

87 ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት የእህል ቍርባናቸውን ጨምሮ ድምራቸው፦ ዐሥራ ሁለት ወይፈን፣ ዐሥራ ሁለት አውራ በግ፣ ዐሥራ ሁለት አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሆነ፤ እንዲሁም ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

87 የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዐሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ከእህሉ ቁርባን ጋር ነበሩ፤ የኃጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

87 ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረበው የከብት ብዛት ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፥ ዐሥራ ሁለት አውራ በጎች፥ ባለ አንድ ዓመት ዕድሜ የሆኑ ዐሥራ ሁለት ተባት በጎች ከእህል ቊርባናቸው ጋርና ዐሥራ ሁለት ተባት ፍየሎች ለኃጢአት መሥዋዕት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

87 የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ከእህሉ ቍርባን ጋር አሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ አሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ አሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ነበሩ፤ የኃጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች አሥራ ሁለት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 7:87
2 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕጣ​ንም የተ​ሞሉ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭ​ል​ፋ​ዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ።


የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደ​ሮች፥ ስድ​ሳም አውራ በጎች፥ ስድ​ሳም አውራ ፍየ​ሎች፥ ስድ​ሳም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ። መሠ​ዊ​ያው ከተ​ቀባ በኋላ ለመ​ቀ​ደ​ሻው የቀ​ረበ ቍር​ባን ይህ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች