Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 7:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለመ​ባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞ​ሉ​ትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የብር ድስት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ለመባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነውን አንድ ጐድጓዳ ሳሕን አቀረበ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለመባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ድስት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 7:19
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስዋም በእናትዋ ተመክራ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ፤” አለችው።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የይ​ሳ​ኮር አለቃ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል አቀ​ረበ።


ዕጣ​ንም የተ​ሞ​ላ​ውን ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆ​ነ​ውን አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤


ለማ​ፍ​ሰ​ሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭ​ቶ​ች​ዋን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ መቅ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ች​ዋ​ንም አድ​ርግ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ር​ጋ​ቸው።


“ማና​ቸ​ውም ሰው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ቢያ​ቀ​ርብ፥ ቍር​ባኑ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይ​ትም ያፈ​ስ​ስ​በ​ታል፤ ነጭ ዕጣ​ንም ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ይህም መሥ​ዋ​ዕት ነው።


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወ​ርቅ ሳሕ​ኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕ​ኖች፥ ሃያ ዘጠ​ኝም ቢላ​ዋ​ዎች፥ ሠላሳ የወ​ርቅ ዳካ​ዎች፥


ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ድስ​ቶ​ችን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኵራ ላይ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ተብሎ ይጻፋል፣ በእግዚአብሔርም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ፤” ብላ ለመነችው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች