Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከወ​ይን ጠጅና ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ ራሱን የተ​ለየ ያድ​ርግ፤ ከወ​ይን ወይም ከሌላ ከሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር የሚ​ገ​ኘ​ውን ሆም​ጣጤ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም ጭማቂ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም እሸት ወይም ዘቢብ አይ​ብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከወይን ጠጅና ከሌላም ከሚያሰክር መጠጥ ይታቀብ፤ የወይንም ሆነ የሚያሰክር የሌላ መጠጥ ሖምጣጤ አይጠጣ፤ እንዲሁም የወይን ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፤ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የሚሠራን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ ማንኛውንም ዓይነት የወይን ዘለላ ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ዘለላ ወይም ዘቢብ አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የወይን ጠጅም ሆነ ማናቸውንም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የተሠራ ሆምጣጤ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 6:3
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እን​ዳ​ት​ሞቱ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ስት​ገቡ ወይም ወደ መሠ​ዊ​ያው ስት​ቀ​ርቡ አን​ተና ልጆ​ችህ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርን ነገር ሁሉ አት​ጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤


ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ነቢ​ያ​ትን፥ ከጐ​በ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! ይህ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“እና​ንተ ግን ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን የወ​ይን ጠጅ አጠ​ጣ​ች​ኋ​ቸው፤ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ “ትን​ቢ​ትን አት​ና​ገሩ ብላ​ችሁ ከለ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸው።


ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ከወ​ይን የሆ​ነ​ውን ነገር ሁሉ ከው​ስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ደረ​ቀው ዘቢብ ድረስ አይ​ብላ።


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።


ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውሃ ብቻ አትጠጣ።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


ከወ​ይ​ንም ከሚ​ወ​ጣው ሁሉ አት​ብላ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጣ፤ ርኩ​ስ​ንም ነገር ሁሉ አት​ብላ፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ትን ሁሉ ጠብቁ” አለው።


አሁ​ንም ተጠ​ን​ቀቂ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጪ፤ ርኩ​ስም ነገር አት​ብዪ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች