Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮች ሁሉ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ለካ​ህኑ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እስራኤላውያን የሚያመጧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ሁሉ ለተቀባዩ ካህን ይሆናሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የእስራኤልም ልጆች ለካህኑ የሚያቀርቡትን ማናቸውም የተቀደሱ ነገሮች ስጦታ ሁሉ ለእርሱ ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ልዩ ስጦታ ሁሉ ስጦታውን ለሚቀበለው ካህን ድርሻ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእስራኤልም ልጆች ለካህኑ የሚያቀርቡት የተቀደሰ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለእርሱ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:9
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም የተ​ለየ ቍር​ባን ነውና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ል​ጆች ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አዝ​ዞ​ኛ​ልና፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን ለአ​ን​ተም፥ ለል​ጆ​ች​ህም የተ​ሰጠ ሥር​ዐት ነውና በቅ​ዱስ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።


እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ወር​ችና ፍር​ምባ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት የእ​ሳት ቍር​ባን ከሆ​ነው ስብ ጋር ያመ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ለአ​ንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ለወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”


የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል።


ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ቀኝ ወር​ቹን ለማ​ን​ሣት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለካ​ህኑ ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ቸሁ።


ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ዩ​ትን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ይህም ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግና የሁ​ል​ጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትን ግብር ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ሰጠው።


ነገር ግን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ ሰው​ዬው ዘመድ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ በደል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​መ​ል​ሰው ነገር ለካ​ህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስ​ተ​ስ​ረያ ከሚ​ደ​ረ​ግ​በት አውራ በግ ላይ ይጨ​መር።


ነገር ግን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገ​ር​ህን፥ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይዘህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ በዚያ እን​ዲ​ጠራ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ሂድ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች