Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “በባ​ልዋ ላይ ለበ​ደ​ለ​ችና ራስ​ዋን ላረ​ከ​ሰች ሴት የቅ​ን​ዐት ሕግ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ ‘እንግዲህ የቅናት ሕግ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በትዳር ላይ እያለች ወደ ሌላ ሄዳ ከረከሰች፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 “ሚስት በባልዋ ሥልጣን ሥር እያለች እርሱን ትታ ፈቀቅ በማለት ራስዋን በምታረክስ ጊዜ ያለው የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29-30 “አንድ ሰው ሚስቱ በእርሱ ላይ እንዳመነዘረችበት ቢጠረጥርና ቅናት ቢያድርበት የሚፈጽመው የሕግ ሥርዓት የሚከተለው ነው፦ ይኸውም ሴትዮዋን በመሠዊያው ፊት ለፊት እንድትቆም ያደርግና ካህኑ ከላይ የተጠቀሰውን ሥርዓት ይፈጽምባታል፤ ወይም የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢያድርና ሚስቱን ቢጠራጠር ወደ መሠዊያው ፊት አምጥቶአት ካህኑ ይህን የሕግ ሥርዓት ይፈጽምባት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29-30 ሴት ባልዋን ትታ በረከሰች ጊዜ፥ ወይም በሰው ላይ የቅንዓት መንፈስ በመጣበት ጊዜ፥ ስለ ሚስቱም በቀና ጊዜ፥ የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤ ሴቲቱንም በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፥ ካህኑም እንደዚህ ሕግ ሁሉ ያድርግባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:29
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰይ​ፋ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ ቆማ​ች​ኋል፤ ርኩስ ነገ​ርን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሚስ​ቶች ታስ​ነ​ው​ራ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን? ስለ​ዚ​ህም እን​ዲህ በላ​ቸው፦


“የእ​ን​ስ​ሳና የወፍ፥ በው​ኃ​ውም ውስጥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።


“በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተ​ልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለ​ምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የማ​ን​ኛ​ውም ሰው ሚስት ከእ​ርሱ ፈቀቅ ብትል፥ በእ​ር​ሱም ላይ ብት​በ​ድል፥


ያ ሰው ሚስ​ቱን ወደ ካህኑ ያም​ጣት፤ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዐሥ​ረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍር​ባን ስለ እር​ስዋ ያምጣ፤ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ነውና፥ ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ያ​ሳ​ስብ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን ነውና ዘይት አያ​ፍ​ስ​ስ​በት፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በት።


ካህ​ኑም ያም​ላ​ታል፤ ሴቲ​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ታል፦ ሌላ ወንድ አል​ተ​ኛሽ፥ ባል​ሽ​ንም አል​ተ​ውሽ፥ ራስ​ሽ​ንም አላ​ረ​ከ​ስሽ እንደ ሆነ፥ ርግ​ማ​ንን ከሚ​ያ​መጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤


ራስ​ዋን ያላ​ረ​ከ​ሰች እንደ ሆነች፥ ያለ ነው​ርም እንደ ሆነች፥ ያነ​ጻ​ታል፤ ልጆ​ች​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች።


በሰው ላይ የቅ​ን​ዐት መን​ፈስ ቢመጣ፥ ስለ ሚስ​ቱም ቢቀና፤ ሴቲ​ቱን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ታል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች