Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን በመ​ር​ገም መሐላ ያም​ላ​ታል፤ ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን እን​ዲህ ይበ​ላት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ረ​ገ​ምሽ ያድ​ር​ግሽ ጎን​ሽን ያረ​ግ​ፈው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝ​ብሽ መካ​ከል ለይቶ ያጥ​ፋሽ፤ ሆድ​ሽን ይሰ​ን​ጥ​ቀው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እዚህ ላይ ካህኑ እንዲህ በማለት ሴትዮዋን በርግማን መሐላ ያስምላታል፤ “እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለለና ሆድሽን እያሳበጠ በሕዝብሽ መካከል ርግማንና መሐላ ያድርግብሽ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይላታል፦ ‘ጌታ ጭንሽን እያመነመነ ሆድሽንም እየነፋ፥ በሕዝብሽ መካከል ጌታ ለመርገምና ለመሐላ የምትሆኚ ያድርግሽ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ካህኑ ሴቲቱን እንዲህ ብሎ የመርገም መሐላ ያስሞላት፦ ‘እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለና ሆድሽን እየነፋ በሕዝብሽ መካከል ለመሓላና ለእርግማን የተገባሽ ያድርግሽ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን፦ እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለ ሆድሽንም እየነፋ፥ እግዚአብሔር ለመርገምና ለመሐላ በሕዝብሽ መካከል ያድርግሽ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:21
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።


ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም።


በዚ​ያ​ችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህ​ችን ከተማ ኢያ​ሪ​ኮን ለመ​ሥ​ራት የሚ​ነሣ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠ​ረ​ቷን በበ​ኵር ልጁ የሚ​ጥል፥ በሮ​ች​ዋ​ንም በታ​ናሹ ልጁ የሚ​ያ​ቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በባ​ቢ​ሎን ያሉ የይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ሳት እንደ ጠበ​ሳ​ቸው እንደ ሴዴ​ቅ​ያ​ስና እንደ አክ​ዓብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ር​ግህ የም​ት​ባል ርግ​ማ​ንን ያነ​ሣሉ፤


በዚያን ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ራሱን ሊረግምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።


ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


አን​ተም ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀ​ትህ በየ​ዕ​ለቱ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በክፉ የአ​ን​ጀት ደዌ ትታ​መ​ማ​ለህ።”


ውኃ​ውን ካጠ​ጣት በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ራስ​ዋን አር​ክ​ሳና ባል​ዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመ​ር​ገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገ​ባል፤ ሆድ​ዋ​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ጎኗም ይረ​ግ​ፋል፤ ሴቲ​ቱም በሕ​ዝ​ብዋ መካ​ከል ለመ​ር​ገም ትሆ​ና​ለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች