Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ካህ​ኑም ያም​ላ​ታል፤ ሴቲ​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ታል፦ ሌላ ወንድ አል​ተ​ኛሽ፥ ባል​ሽ​ንም አል​ተ​ውሽ፥ ራስ​ሽ​ንም አላ​ረ​ከ​ስሽ እንደ ሆነ፥ ርግ​ማ​ንን ከሚ​ያ​መጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ካህኑም ሴትዮዋን ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፤ “ሌላ ወንድ ዐብሮሽ ካልተኛ፣ በትዳር ላይ ሆነሽ ወደ ርኩሰት ካላዘነበልሽ ይህ ርግማን የሚያመጣ መራራ ውሃ ጕዳት አያድርስብሽ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሴቲቱንም እንዲህ ብሎ ካህኑ ያምላታል፦ ‘ከአንቺ ጋር ሌላ ወንድ ካልተኛ፥ በባልሽም ሥልጣን ሥር እየነበርሽ ራስሽን ለማርከስ ዘወር ካላልሽ፥ እርግማንን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውኃ የተጠበቅሽ ሁኚ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚያም ካህኑ እንዲህ ብሎ ያስምላት፦ ከባልሽ ጋር እያለሽ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የተኛ ባይሆን፥ ራስሽንም ባታረክሺ ርግማን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውሃ ነጻ ሁኚ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ካህኑም ያምላታል፥ ሴቲቱንም እንዲህ ይላታል፦ ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ እንደ ሆነ፥ እርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:19
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የማ​ን​ኛ​ውም ሰው ሚስት ከእ​ርሱ ፈቀቅ ብትል፥ በእ​ር​ሱም ላይ ብት​በ​ድል፥


ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ታል፤ የሴ​ቲ​ቱ​ንም ራስ ይገ​ል​ጣል፤ በእ​ጅ​ዋም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ህል ቍር​ባን፥ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ያኖ​ራል፤ በካ​ህ​ኑም እጅ ርግ​ማ​ንን የሚ​ያ​መ​ጣው መራራ ውኃ ይሆ​ናል።


ራስ​ዋን ያላ​ረ​ከ​ሰች እንደ ሆነች፥ ያለ ነው​ርም እንደ ሆነች፥ ያነ​ጻ​ታል፤ ልጆ​ች​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።


ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ከእ​ርሱ ጋር በሕግ የታ​ሰ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚ​ስ​ት​ነት ታስ​ራ​በት ከኖ​ረ​ችው ሕግ የተ​ፈ​ታች ናት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች