Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ታል፤ የሴ​ቲ​ቱ​ንም ራስ ይገ​ል​ጣል፤ በእ​ጅ​ዋም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ህል ቍር​ባን፥ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ያኖ​ራል፤ በካ​ህ​ኑም እጅ ርግ​ማ​ንን የሚ​ያ​መ​ጣው መራራ ውኃ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ካህኑ ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ካደረገ በኋላ የጠጕሯን መሸፈኛ ይገልጣል፤ ስለ ቅናት የቀረበውን የመታሰቢያ ቍርባን በእጇ ያስይዛታል፤ ከዚያም ካህኑ ርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ በእጁ ይይዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ካህኑም ሴቲቱን በጌታ ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም የተሠራ ጠጉር ይፈታል፥ በእጅዋም የመታሰቢያ የእህል ቁርባን የሆነውን የቅንዓት የእህል ቁርባን ያኖራል፤ ካህኑም እርግማንን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፥ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ ለቅንዓት ቍርባን፥ ያኖራል፤ በካህኑም እጅ እርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:18
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ሴት ካል​ተ​ከ​ና​ነ​በች ትላጭ ወይም ጠጕ​ር​ዋን ትቈ​ረጥ፤ ለሴት ጠጕ​ር​ዋን መቈ​ረጥ ወይም መላ​ጨት ውር​ደት ከሆነ ትከ​ና​ነብ።


ክፋ​ትሽ ይገ​ሥ​ጽ​ሻል፤ ክዳ​ት​ሽም ይዘ​ል​ፍ​ሻል፤ እኔን መተ​ው​ሽም ክፉና መራራ ነገር መሆ​ኑን ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትረ​ጂ​ማ​ለሽ” ይላል አም​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “መፈ​ራ​ቴም በአ​ንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላ​ሰ​ኘ​ኝም” ይላል አም​ላ​ክሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ ይቅር አል​ሃት፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሁሉ ወደ ኋላዬ ጣልህ።


እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል።


ፍጻሜው ግን እንደ ሐሞት የመረረ ነው፥ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅም የተሳለ ነው።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግን አም​ጡ​ልኝ” አለ። አጋ​ግም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋ​ግም፥ “በውኑ ሞት እን​ደ​ዚህ መራራ ነውን?” አለ።


ሄዶ የእ​ነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያመ​ልክ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡን ዛሬ የሚ​ያ​ስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ሐሞ​ትና እሬ​ትም የሚ​ያ​በ​ቅል ሥር አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ።


ርግ​ማ​ን​ንም የሚ​ያ​መጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅ​ፀ​ን​ሽ​ንም ይሰ​ን​ጥ​ቀው፤ ጎን​ሽም ይር​ገፍ። ሴቲ​ቱም፦ ይሁን ይሁን ትላ​ለች።


ካህ​ኑም የተ​ቀ​ደሰ ውኃ በሸ​ክላ ማሰሮ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ካለው ትቢያ ወስዶ በውኃ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤


ያ ሰው ሚስ​ቱን ወደ ካህኑ ያም​ጣት፤ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዐሥ​ረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍር​ባን ስለ እር​ስዋ ያምጣ፤ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ነውና፥ ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ያ​ሳ​ስብ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን ነውና ዘይት አያ​ፍ​ስ​ስ​በት፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በት።


“የለ​ምጽ ደዌ ያለ​በት ሰው ልብሱ የተ​ቀ​ደደ ይሁን፤ ራሱም የተ​ገ​ለጠ ይሁን፤ ከን​ፈ​ሩ​ንም ይሸ​ፍን፤ ርኩስ ይባ​ላል።


ለሴት ግን ጠጕ​ር​ዋን ብታ​ሳ​ድግ ክብ​ርዋ ነው፤ ለሴት ጠጕ​ርዋ እንደ ቀጸላ ሆኖ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ታ​ልና።


ካህ​ኑም ያም​ላ​ታል፤ ሴቲ​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ታል፦ ሌላ ወንድ አል​ተ​ኛሽ፥ ባል​ሽ​ንም አል​ተ​ውሽ፥ ራስ​ሽ​ንም አላ​ረ​ከ​ስሽ እንደ ሆነ፥ ርግ​ማ​ንን ከሚ​ያ​መጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች