Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ያ ሰው ሚስ​ቱን ወደ ካህኑ ያም​ጣት፤ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዐሥ​ረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍር​ባን ስለ እር​ስዋ ያምጣ፤ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ነውና፥ ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ያ​ሳ​ስብ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን ነውና ዘይት አያ​ፍ​ስ​ስ​በት፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ወደ ካህኑ ይውሰዳት፤ ስለ እርሷም አንድ ኪሎ ገብስ ዱቄት ለቍርባን ይውሰድ፤ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ ይህ ስለ ቅናት የቀረበ የእህል ቍርባን በደልን የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ የገብስ ዱቄት የሆነውን ስለ እርሷ የሚቀርበውን ቁርባን ያምጣ፤ የቅንዓት የእህል ቁርባን ነውና፥ በደልንም የሚያስታውስ የመታሰቢያ የእህል ቁርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ ስለ እርስዋ የሚፈልገውንም አንድ ኪሎ የገብስ ዱቄት ቊርባን ያምጣ፤ የቅናት ቊርባን ማለት በደልን የሚገልጥ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዓት ቍርባን ነውና፥ ኃጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:15
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።


እርሱ በፊ​ታ​ቸው ምዋ​ር​ትን ያም​ዋ​ር​ታል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ዐስቦ ሰባት ሱባዔ ይቈ​ጥ​ር​ባ​ቸ​ዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እነ​ር​ሱን በተ​ከ​ተሉ ጊዜ እር​ስዋ በደ​ልን ታሳ​ስ​ባ​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ መታ​መኛ አት​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


እኔም በዐ​ሥራ አም​ስት ብርና በአ​ንድ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ተኩል ገብ​ስና በአ​ንድ ፊቀን ወይን ተወ​ዳ​ጀ​ኋት።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቢኖር መባ​ች​ሁን ከእ​ን​ስሳ ወገን ከላ​ሞች ወይም ከበ​ጎች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


“ማና​ቸ​ውም ሰው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ቢያ​ቀ​ርብ፥ ቍር​ባኑ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይ​ትም ያፈ​ስ​ስ​በ​ታል፤ ነጭ ዕጣ​ንም ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ይህም መሥ​ዋ​ዕት ነው።


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


“ካህ​ኑም ያቀ​ር​ባ​ታል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ያቆ​ማ​ታል፤


ነገር ግን በዚ​ያው መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዓ​መቱ የኀ​ጢ​አት መታ​ሰ​ቢያ አድ​ር​ገው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ነበ​ራ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች