Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ በአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስጥ ያድ​ርጉ፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም ይህንና ከዚሁ ጋራ የተያያዙትን ዕቃዎች ሁሉ በአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ ጠቅልለው በመሸከሚያ ሳንቃ ላይ ያስቀምጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 መቅረዙንና የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያኑሩት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መቅረዙንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ በቈዳ መሸፈኛ ጠቅልለው በመሸከሚያ ተራዳ ላይ ያኑሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እርሱንና ዕቃዎቹን ሁሉ በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 4:10
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“መቅ​ረ​ዝ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ርግ፤ የመ​ቅ​ረ​ዙም እግ​ሩና ቅር​ን​ጫ​ፎቹ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋ​ዎ​ቹም፥ ጕብ​ጕ​ቦ​ቹም፥ አበ​ቦ​ቹም አን​ድ​ነት በእ​ርሱ ይደ​ረ​ጉ​በት።


የፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ቀይ የተ​ለፋ የአ​ውራ በግ ቍር​በት፥ ሰማ​ያዊ ቀለም የገባ ቍር​በት፥ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት፥


በወ​ር​ቁም መሠ​ዊያ ላይ ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ።


በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን የማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ይው​ሰዱ፤ በሰ​ማ​ያ​ዊ​ዉም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ውስጥ ያስ​ቀ​ም​ጡት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።


በላ​ዩም የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ያድ​ር​ጉ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በላይ ሁለ​ን​ተ​ናው ሰማ​ያዊ የሆነ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ያግ​ቡ​በት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግ​ቡ​በት።


ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይው​ሰዱ፤ የሚ​ያ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም መቅ​ረዝ፥ ቀን​ዲ​ሎ​ች​ዋ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል የዘ​ይ​ቱን ማሰ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሸ​ፍኑ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች