Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 33:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከራ​ምሴ ተጓዙ፤ ከፋ​ሲካ በኋላ በነ​ጋው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ፊት ከፍ ባለች እጅ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብጻውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አምስተኛው ቀን ከራዓምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በማግስቱ የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር የወጡት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የፋሲካ በዓል ማግስት ነበር። ግብጻውያን ሁሉ ፊት ለፊት እያዩአቸው በእግዚአብሔር ጠባቂነት የራምሴን ከተማ ለቀው ወጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 33:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጸና፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አሳ​ደደ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ።


እና​ንተ በዚች ቀን በሚ​ያ​ዝያ ወር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።


ንጹሕ ደም​ንም አፈ​ሰሱ፥ የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ደም፥ ለከ​ነ​ዓን ጣዖ​ቶች ሠዉ፥ ምድ​ርም በደም ታለ​ለች።


“ይህ ወር የወ​ሮች መጀ​መ​ሪያ ይሁ​ና​ችሁ፤ የዓ​መ​ቱም መጀ​መ​ሪያ ወር ይሁ​ና​ችሁ።


ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።


በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እንደ ተጓዙ የሰ​ፈ​ሩ​በ​ትን ጻፈ፥ እየ​ተ​ጓዙ ያደ​ሩ​በት ይህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች