Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 32:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 የም​ና​ሴም ልጅ ኢያ​ዕር ሄዶ መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ፤ የኢ​ያ​ዕ​ርም መን​ደ​ሮች ብሎ ጠራ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር መኖሪያቸውን ወስዶ፣ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮቻቸውን ያዘ፥ እነርሱንም የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ከምናሴ ነገድ የሆነው ያኢር በአንዳንድ መንደሮች ላይ አደጋ ጥሎ ወሰዳቸው፤ “የያኢር መንደሮች” ብሎም ሰየማቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮችዋን ወሰደ፥ የኢያዕርም መንደሮች ብሎ ጠራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 32:41
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የም​ናሴ ልጅ ኢያ​ዕር እስከ ጌር​ጋ​ሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ች​ንም የባ​ሳ​ንን ምድር እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በስሙ አው​ታይ ኢያ​ዕር ብሎ ጠራ።


በሠ​ላሳ ሁለት የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ይቀ​መጡ የነ​በሩ ሠላሳ ሁለት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች የተ​ባሉ በገ​ለ​ዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተ​ሞች ነበ​ሩ​አ​ቸው።


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ና​ይም ጀምሮ የባ​ሳን ንጉሥ የዐግ መን​ግ​ሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባ​ሳ​ንም ያሉት የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ሁሉ ስድ​ሳው ከተ​ሞች፥ የገ​ለ​ዓ​ድም እኩ​ሌታ፥


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች