Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 32:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ባይ​ሻ​ገሩ ግን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ንዱ​አ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ና​ንተ መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ለጦርነት ተዘጋጅተው ከእናንተ ጋራ ካልተሻገሩ ግን፣ ርስታቸውን ዐብረዋችሁ በከነዓን መካፈል አለባቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ለጦርነት ተዘጋጅተው ከእናንተ ጋር ባይሻገሩ ግን በከነዓን ምድር በእናንተ መካከል ርስታቸውን ይወርሳሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ዮርዳኖስን ተሻግረው ከእናንተ ጋር ወደ ጦርነት የማይሄዱ ከሆነ ግን ልክ እንደ እናንተው በከነዓን ምድር የራሳቸው ድርሻ የሆነ ርስት ይሰጣቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር ባይሻገሩ ግን በከነዓን ምድር በእናንተ መካከል ርስታቸውን ይወርሳሉ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 32:30
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መል​ሰው፥ “ጌታ​ችን ለእኛ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


ነገር ግን የር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቢያ​ን​ሳ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ምድር አል​ፋ​ችሁ ከእኛ ጋር ውረሱ፤ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጭ ለእ​ና​ንተ መሠ​ዊያ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ካዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አት​ተ​ዉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች