Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 32:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ይህን ባታደርጉ ግን እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኀጢአታችሁ እንደሚያገኛችሁም ዕወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርታችኋል፤ ኃጢአታችሁም በእውነት እንደሚያገኛችሁ እወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኃጢአታችሁም እንዲያገኛችሁ እወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 32:23
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐመ​ፃ​ችን በአ​ንተ ፊት በዝ​ቶ​አ​ልና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም መስ​ክ​ሮ​ብ​ና​ልና፥ ዐመ​ፃ​ችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም አላ​ወ​ቅ​ን​ምና።


በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


ይሁ​ዳም አለ፦ “ለጌ​ታ​ችን ምን እን​መ​ል​ሳ​ለን? ምንስ እን​ና​ገ​ራ​ለን? ወይስ በምን እን​ነ​ጻ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ኀጢ​አት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእ​ርሱ ዘንድ የተ​ገ​ኘ​በ​ትም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነን።”


በዐ​ይ​ኖ​ችህ ብቻ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ፍዳ ታያ​ለህ።


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


በእ​ው​ነት ያመ​ጣ​ህ​ልኝ አይ​ደ​ለም፤ አግ​ባ​ብስ በእ​ው​ነት ታመ​ጣ​ልኝ ዘንድ ነበር። በደ​ልህ፤ እን​ግ​ዲህ ዝም በል፤ የወ​ን​ድ​ምህ መመ​ለ​ሻው ወደ አንተ ነው፤ አን​ተም ትሰ​ለ​ጥ​ን​በ​ታ​ለህ።”


መከ​ራና ጭን​ቀት አስ​ቀ​ድሞ በአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም በአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ ክፉ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ ነው።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


ተና​ጋሪ ሰው በም​ድር ውስጥ አይ​ጸ​ናም፤ ዐመ​ፀኛ ሰውን ክፋት ለጥ​ፋት ታድ​ነ​ዋ​ለች።


የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ።


በዘ​ን​በ​ሪም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዘ​ን​በ​ሪም ቤተ ሰብ እያ​ን​ዳ​ንዱ ተለየ፤ ከይ​ሁ​ዳም ወገን በሆነ በከ​ርሚ ልጅ በዘ​ን​በሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአ​ካን ላይ ምል​ክት ታየ።


ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ።


እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።


አባቴ ዳዊት ሳያ​ውቅ ከእ​ርሱ የሚ​ሻ​ሉ​ትን ሁለ​ቱን ጻድ​ቃን ሰዎች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሠራ​ዊት አለቃ የኔ​ርን ልጅ አበ​ኔ​ርን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሠራ​ዊት አለቃ የኢ​ያ​ቴ​ርን ልጅ አሜ​ሳ​ይን በሰ​ይፍ ገድ​ሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዐ​መፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።


ደማ​ቸ​ውም በኢ​ዮ​አብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ፤ ለዳ​ዊት ግን ለዘ​ሩና ለቤቱ፥ ለዙ​ፋ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሁን።”


ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ሰባት ጊዜም ይነሣል። ኃጥኣን ግን በክፉ ደዌ ይያዛሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች