Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሙሴና አሮ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዛ​ቸው ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል በታዘዘው መሠረት እነዚህን ቈጠራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሙሴም እንደ ጌታ ቃል፥ እንደ ታዘዘው ቈጠራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሙሴም በእግዚአብሔር ቃል እንደታዘዘው ቈጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው ቈጠራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:16
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የሚ​ገ​ቡት ሁሉ፥ የቀ​ዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው፥ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወን​ዶች ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ሃያ ሁለት ሺህ ነበሩ።


የሌዊ ልጆች ካህ​ና​ትም ይቀ​ር​ባሉ፤ በፊቱ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ በስ​ሙም እን​ዲ​ባ​ርኩ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ በእ​ነ​ር​ሱም ቃል ክር​ክር ሁሉ ጕዳ​ትም ሁሉ ይቆ​ማ​ልና፤


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሸ​ክ​ማ​ቸው በሙሴ እጅ ተቈ​ጠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በእ​ርሱ ተቈ​ጠሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች ቍጥር ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ገ​ሉት ሁሉ የጌ​ድ​ሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው።


የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ፥ በተ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ፥ በሥ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ትእ​ዛዝ ይሁን፤ በስ​ማ​ቸ​ውና በተ​ራ​ቸ​ውም ትቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ሰጠ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ዮሴ​ፍም የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን እንደ ነገ​ረው ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ለመ​ን​ገድ ስን​ቅን ሰጣ​ቸው፤


“የሌ​ዊን ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ቍጠር፤ ወን​ዱን ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ቍጠ​ራ​ቸው።”


የሌዊ ልጆች በየ​ስ​ማ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች