Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 28:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በእ​ሳ​ትም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንከን የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ለጌታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፤ እነርሱም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን ተመልከቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይኸውም ነውር የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፤ ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 28:19
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነው​ረኛ ወይም አን​ካሳ ወይም ዕውር ቢሆን፥ ወይም አን​ዳች ክፉ ነውር ቢኖ​ረው፥ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠ​ዋው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ሌላ እነ​ር​ሱ​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁኑ።


ነገር ግን አይ​ሠ​ም​ር​ላ​ች​ሁ​ምና ነውር ያለ​በ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ።


የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ንድ ወይ​ፈን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥


“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ከበ​ግና ከላም መንጋ ሠዋ።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ ክፍ​ላ​ቸው ለሕ​ዝቡ ልጆች እን​ዲ​ሰጡ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለዩ። እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎቹ አደ​ረጉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች