Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 26:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከሃያ ዓመት ጀምሮ፥ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ሕዝብ ቍጠሩ።” ከግ​ብፅ ምድር የወጡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።” ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቁጠሩ።” ከግብጽም ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።” ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔር ሙሴን ከግብፅም ምድር የወጡትን የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዛቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝቡን ቍጠሩ ብለው ተናገሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 26:4
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​ባ​ታ​ቸው ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ሮቤል።


ያን​ጊ​ዜም ሰይ​ጣን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቈ​ጥር ዘንድ ዳዊ​ትን አነ​ሣ​ሣው።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦


የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር ሮቤል፤ የሮ​ቤል ልጆች፤ ከሄ​ኖኅ የሄ​ኖ​ኃ​ው​ያን ወገን፤ ከፈ​ሉስ የፈ​ሉ​ሳ​ው​ያን ወገን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች