Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ማኅ​በ​ሩም በሞቱ ጊዜ ምድ​ሪቱ አፍ​ዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠ​ቻ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ እሳ​ቲቱ ሁለት መቶ አም​ሳ​ውን ሰዎች አቃ​ጠ​ለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለም​ል​ክት ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሁለት መቶ ዐምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከርሱ ጋራ ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ያም ወገን በሞተ ጊዜ፥ እሳቲቱም ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች ባቃጠለች ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ እነርሱን ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነርሱንም ምድር ተከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እሳት ወርዶ ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች አቃጠላቸው፤ ለሕዝቡም መቀጣጫ ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ያም ወገን በሞተ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 26:10
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”


ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥


እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


ፊቴ​ንም በዚያ ሰው ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ጠ​ፋም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በባ​ቢ​ሎን ያሉ የይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ሳት እንደ ጠበ​ሳ​ቸው እንደ ሴዴ​ቅ​ያ​ስና እንደ አክ​ዓብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ር​ግህ የም​ት​ባል ርግ​ማ​ንን ያነ​ሣሉ፤


ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ።


በሙ​ሴም ላይ ተነሡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ክር የተ​መ​ረጡ፥ ዝና​ቸ​ውም የተ​ሰማ ሁለት መቶ አምሳ የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።


“አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ምድር እስ​ከ​ሚ​መጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መካ​ከል ምድር አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ በዋ​ጠ​ቻ​ቸው በሮ​ቤል ልጅ በኤ​ል​ያብ ልጆች በዳ​ታ​ንና በአ​ቤ​ሮን ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፤


በአ​ን​ተም በልጅ ልጅ​ህም ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለም​ል​ክ​ትና ለድ​ንቅ ይሆ​ናሉ።


ለየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ወገን አንድ በትር ይሰ​ጣ​ሉና በሌዊ በትር ላይ የአ​ሮ​ንን ስም ጻፍ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች