Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ደ​ሚ​ጋ​ርዱ ዛፎች፥ በወ​ንዝ ዳር እን​ዳሉ የተ​ክል ቦታ​ዎች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተከ​ላ​ቸው ድን​ኳ​ኖች በው​ኃም ዳር እን​ዳሉ ዝግ​ባ​ዎች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “እንደ ሸለቆዎች፣ በወንዝ ዳር እንዳሉም የአትክልት ስፍራዎች ተዘርግተዋል፤ በእግዚአብሔር እንደ ተተከሉ አደሶች፣ በውሃም አጠገብ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ወደፊትም ተዘርግቶ እንዳለው ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ ጌታ እንደ ተከለው ዓልሙን በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነርሱም እንደ ተዘረጉ ሸለቆዎችና፥ በወንዝ ዳር እንደሚገኙ የአትክልት ቦታዎች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከለው የሬት ዛፍ ወይም በውሃ ዳር እንደ በቀለ የሊባኖስ ዛፍ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንደ ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከለው እሬት በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 24:6
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።


እር​ሱም በውኃ ፈሳ​ሾች ዳር እንደ ተተ​ከ​ለች፥ ፍሬ​ዋን በየ​ጊ​ዜዋ እን​ደ​ም​ት​ሰጥ፥ ቅጠ​ል​ዋም እን​ደ​ማ​ይ​ረ​ግፍ ዛፍ ይሆ​ናል፤ የሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል።


በም​ድር ላይ ራብን አመጣ፥ የእ​ህ​ልን ኀይል ሁሉ አጠፋ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በም​ድር ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት እን​ድ​ታዩ ኑ።


ልጅ ወን​ድሜየወ​ን​ዙን ዳር ልም​ላሜ ያይ ዘንድ ወይኑ አብቦ ሮማ​ኑም አፍ​ርቶ እንደ ሆነ ይመ​ለ​ከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ።


በም​ድረ በዳ ዝግ​ባ​ው​ንና ግራ​ሩን፥ ባር​ሰ​ነ​ቱ​ንና የዘ​ይ​ቱን ዛፍ አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁል​ጊዜ ከአ​ንተ ጋር ይኖ​ራል፤ እንደ ነፍ​ስ​ህም ፍላ​ጎት ያጠ​ግ​ብ​ሃል፤ አጥ​ን​ት​ህ​ንም ያለ​መ​ል​ማል፤ አን​ተም እን​ደ​ሚ​ጠጣ ገነት፥ ውኃ​ውም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ምንጭ ትሆ​ና​ለህ።


አሳ​ዳ​ጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አል​ፈር፤ እነ​ርሱ ይደ​ን​ግጡ፤ እኔ ግን አል​ደ​ን​ግጥ፤ ክፉ​ንም ቀን አም​ጣ​ባ​ቸው፤ በሁ​ለት እጥፍ ጥፋት ቀጥ​ቅ​ጣ​ቸው።


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ በዳሩ ላይ በዚ​ህና በዚያ ፍሬው የሚ​በላ ዛፍ ሁሉ ይበ​ቅ​ላል፤ ቅጠ​ሉም አይ​ረ​ግ​ፍም፤ ፍሬ​ውም አይ​ጐ​ድ​ልም፤ ውኃ​ውም ከመ​ቅ​ደስ ይወ​ጣ​ልና በየ​ወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገ​ኛል፤ ፍሬ​ውም ለመ​ብል፥ ቅጠ​ሉም ለመ​ድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል።”


“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ተራ​ሮች ማርን ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ወተ​ትን ያፈ​ስ​ሳሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ያሉት ፈፋ​ዎች ሁሉ ውኃን ያጐ​ር​ፋሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ምንጭ ትፈ​ል​ቃ​ለች፤ የሰ​ኪ​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ታጠ​ጣ​ለች።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ ቤቶ​ችህ፥ እስ​ራ​ኤል ሆይ ድን​ኳ​ኖ​ችህ ምንኛ ያም​ራሉ!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች