Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኽ​ብኝ ምን​ድን ነው? ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ፤ እነ​ሆም፥ መባ​ረ​ክን ባረ​ክ​ሃ​ቸው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ያደረግህብኝ ምንድነው? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ባላቅም በለዓምን “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እኔ ወደዚህ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን እነርሱን ከመመረቅ በቀር ምንም አላደረግህም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 23:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእ​ን​ጀ​ራና በውኃ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምና፥ ይረ​ግ​ማ​ቸ​ውም ዘንድ በለ​ዓ​ምን ገዝ​ተ​ው​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችን ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት መለ​ሰው።


ባላ​ቅም በበ​ለ​ዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆ​ቹ​ንም አጨ​በ​ጨበ፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፦ ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግም ዘንድ ጠራ​ሁህ፥


ክብ​ር​ህን እጅግ ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና፥ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገ​ም​ልኝ ብሏል” አሉት።


እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ የም​ድ​ርን ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ዬም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ ምና​ል​ባት እወ​ጋው፥ አሳ​ድ​ደ​ውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁ​ንም ና እር​ሱን ርገ​ም​ልኝ።”


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን መልሶ፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ ያደ​ረ​ገ​ውን እና​ገር ዘንድ የም​ጠ​ነ​ቀቅ አይ​ደ​ለ​ምን?”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች