Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሞዓ​ብም የም​ድ​ያ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “በሬ የለ​መ​ለ​መ​ውን ሣር እን​ደ​ሚ​ጨ​ርስ ይህ ሠራ​ዊት በዙ​ሪ​ያ​ችን ያለ​ውን ሁሉ ይጨ​ር​ሳል” አላ​ቸው። በዚ​ያን ጊዜ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ የሞ​ዓብ ንጉሥ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፦ “በሬ የለመለመውን የሣር መስክ ግጦ እንደሚጨርስ ይህ ጭፍራ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ አሁን ይጨርሳል” አላቸው። በዚያን ጊዜም የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሞአባውያን ለምድያማውያን ሽማግሌዎች “ይህ የምታዩት የሕዝብ ብዛት በሬ በመስክ የሚገኘውን ሣር ሁሉ ጠራርጎ እንደሚበላ በዙሪያችን ያለውን ነገር ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሉአቸው። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የሞአብ ንጉሥ የነበረው የጺጶር ልጅ ባላቅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፦ በሬ የለመለመውን ሣር እንደሚጨርስ ይህ ጭፍራ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ይጨርሳል አላቸው። በዚያን ጊዜም የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 22:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የም​ድ​ያ​ም​ንም ነገ​ሥ​ታት በዚ​ያው ጦር​ነት በአ​ን​ድ​ነት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢ​ዖ​ር​ንም ልጅ በለ​ዓ​ምን ደግሞ በዚ​ያው ጦር​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


ሞአ​ብ​ንም ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም ዕቃ ሰብ​ሬ​አ​ለ​ሁና በሞ​አብ ሰገ​ነት ሁሉ ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወይስ ዛሬ ከሞ​ዓብ ንጉሥ ከሴ​ፎር ልጅ ከባ​ላቅ አንተ ትሻ​ላ​ለ​ህን? ወይስ እርሱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተጣ​ላን? ወይስ ተዋ​ጋ​ውን?


አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


የሞ​ዓብ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የም​ድ​ያም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም የም​ዋ​ር​ቱን ዋጋ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለ​ዓ​ምም መጡ፤ የባ​ላ​ቅ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


የሴ​ፎር ልጅ ባላቅ እስ​ራ​ኤል በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አየ።


ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


እነ​ሆም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙ​ሴና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ፊት ወን​ድ​ሙን ወደ ምድ​ያ​ማ​ዊት ሴት ወሰ​ደው፤ እነ​ር​ሱም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ያለ​ቅሱ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድ​ያም እጅ ሰባት ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ከም​ድ​ያ​ምም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከፋ​ራን ሰዎ​ችን ወሰዱ፤ ወደ ግብ​ፅም መጡ፤ ወደ ግብ​ፅም ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን ሄዱ፤ አዴ​ርም ወደ ፈር​ዖን ገባ። እር​ሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረ​ገው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች