Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 22:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የበ​ለ​ዓ​ምን ዐይ​ኖች ከፈተ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የበለዓምን ዐይን ከፈተ፤ እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ እንደ ያዘ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ፤ ጐንበስ ብሎም በግንባሩ ተደፋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጌታም የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፤ የጌታም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተምዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደ መሬት ተደፋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በለዓም ሰይፍ ይዞ የቆመውን መልአክ ለማየት እንዲችል አደረገው፤ በለዓምም በግንባሩ ወደ መሬት ተደፋ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተምዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 22:31
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ጋር ዐይ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ የውኃ ጕድ​ጓ​ድ​ንም አየች፤ ሄዳም አቍ​ማ​ዳ​ውን በውኃ ሞላች፤ ልጅ​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ችው።


ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


ዐይ​ና​ቸ​ውም ተገ​ለ​ጠና ዐወ​ቁት፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ከእ​ነ​ርሱ ተሰ​ወረ።


እን​ዳ​ያ​ው​ቁ​ትም ዐይ​ና​ቸው ተይዞ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ” ባላ​ቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ል​ሰው በም​ድር ላይ ወደቁ።


አቤቱ፥ የሕግ መም​ህ​ርን በላ​ያ​ቸው ላይ ሹም፤ አሕ​ዛ​ብም ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።


ዳዊ​ትም ዐይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተዘ​ር​ግቶ አየ። ዳዊ​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ማቅ ለብ​ሰው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥ የል​ዑ​ል​ንም ዕው​ቀት የሚ​ያ​ውቅ፥ ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥ ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥ ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥ ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦


ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጎ​ነ​በ​ሰና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፦


አህ​ያ​ዪ​ቱም በለ​ዓ​ምን፥ “ከወ​ጣ​ት​ነ​ትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​ብኝ አህ​ያህ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? በውኑ አን​ተን ቸል ያል​ሁ​በት፥ በአ​ን​ተም እን​ዲህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​በት ጊዜ ነበ​ርን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሽ​ብ​ኝም” አላት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢ​ያ​ሪኮ አጠ​ገብ ሳለ ዐይ​ኑን አን​ሥቶ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ የተ​መ​ዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያ​ሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ወገን ነህ?” አለው።


እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች