Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እር​ሱም ስለ ሄደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ሊያ​ሰ​ና​ክ​ለው ተነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይሁን እንጂ በለዓም በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር በጣም ተቈጥቶ ስለ ነበር የእግዚአብሔር መልአክ ሊቃወመው በመንገዱ ላይ ቆመ። በለዓምም በአህያው ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ሁለት አሽከሮቹም ዐብረው ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ የጌታም መልአክ ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ። እርሱም በአህያይቱ ላይ ሆኖ ይጓዝ ነበር፥ ሁለቱም ሎሌዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በለዓም በመሄዱ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ በለዓም ሁለቱን አሽከሮቹን በማስከተል በአህያው ላይ ተቀምጦ በሚጓዝበት ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ መንገዱን ዘጋበት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሊቍቍመው በመንገድ ላይ ቆመ። እርሱም በአህያይቱ ላይ፥ ሁለቱም ሎሌዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 22:22
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “አህ​ያ​ህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መን​ገ​ድህ በፊቴ ቀና አል​ነ​በ​ረ​ምና ላሰ​ና​ክ​ልህ ወጥ​ቼ​አ​ለሁ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመ​ን​ገድ ላይ በአ​ደ​ረ​በት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ተገ​ና​ኘው፤ ሊገ​ድ​ለ​ውም ፈለገ።


ዳሌጥ። ቀስ​ቱን እንደ ተቃ​ዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላ​ጋ​ራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽ​ዮን ሴት ልጅ ድን​ኳን ለዐ​ይኑ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ሁሉ ገደለ፤ መዓ​ቱ​ንም እንደ እሳት አፈ​ሰሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከጥ​ቂት ዘመን በኋላ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልን ደም በይ​ሁዳ ቤት ላይ እበ​ቀ​ላ​ለ​ሁና፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መን​ግ​ሥ​ትን እሽ​ራ​ለ​ሁና ስሙን ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ብለህ ጥራው፤


ኢዩም፥ “ለበ​ዓል መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አንጹ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዋጅ ነገሩ።


የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።


“በመ​ን​ገድ ይጠ​ብ​ቅህ ዘንድ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ል​ህም ስፍራ ያገ​ባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መል​አ​ኬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ።


እር​ሱም በአ​ህ​ያ​ዪቱ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሁለ​ቱም ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ። አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመ​ን​ገ​ዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለ​ዓ​ምም ወደ መን​ገድ ይመ​ል​ሳት ዘንድ አህ​ያ​ዪ​ቱን መታት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች