Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 22:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ በለ​ዓ​ምም መጥ​ተው፥ “የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እባ​ክህ ወደ እኔ መም​ጣ​ትን ቸል አት​በል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፤ “የሴፎር ልጅ ባላቅ ይህን እንድንነግርህ ልኮናል፤ ወደ እኔ ለመምጣት የሚያግድህ ምንም ነገር አይኑር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ በለዓምም መጥተው እንዲህ አሉት፦ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ፥ ወደ እኔ ለመምጣት ምንም ዓይነት ነገር አያግድህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነርሱም ወደ በለዓም ሄደው የባላቅን መልእክት እንዲህ ሲሉ ነገሩት፤ “ወደ እኔ መምጣት እንዳትችል የሚያግድህ ነገር አይኑር!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16-17 ወደ በለዓምም መጥተው፦ የሴፎር ልጅ ባላቅ፦ ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና፥ እባክህ፥ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ምንም አይከልክልህ፤ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ አለ ብለው ነገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 22:16
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ባላ​ቅም ደግሞ ከእ​ነ​ዚያ የበ​ዙና የከ​በሩ ሌሎ​ችን አለ​ቆች ሰደደ።


ክብ​ር​ህን እጅግ ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና፥ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገ​ም​ልኝ ብሏል” አሉት።


ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “አን​ተን ለመ​ጥ​ራት የላ​ክ​ሁ​ብህ አይ​ደ​ለ​ምን? ለም​ንስ ወደ እኔ አል​መ​ጣ​ህም? አን​ተን ለማ​ክ​በር እኔ አል​ች​ል​ምን?” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች