Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የጊ​ደ​ሪ​ቱ​ንም አመድ ያከ​ማ​ቸው ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የጊደሯን ዐመድ የሚያፈስሰውም ሰው እንደዚሁ ልብሱን ማጠብ አለበት፤ ያም ሰው እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል፤ ይህም ለእስራኤላውያን እንዲሁም በመካከላቸው ለሚኖሩ መጻተኞች የሚሆን ዘላለማዊ ሥርዐት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የጊደሪቱንም አመድ የሰበሰበው ሰው ልብሱን ያጥባል እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ይህም ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ለሚኖር መጻተኛ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዐመዱን የሰበሰበው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ነገር ግን እስከ ማታ ያልነጻ ሆኖ ይቈያል፤ ይህ የሥርዓት መመሪያ ለእስራኤላውያንና በመካከላቸው ለሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ የጸና ሕግ ሆኖ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የጊደሪቱንም አመድ ያከማቸ ሰው ልብሱን ያጥባል እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ይህም ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ለሚኖር መጻተኛ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 19:10
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”


ከእ​ነ​ር​ሱም በድን የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


በተ​ዘ​ጋ​በ​ትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚ​ገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።


ያቃ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል።


ንጹ​ሑም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀንና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በር​ኩሱ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ጻል፤ እር​ሱም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ይህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ውን ውኃ የሚ​ረጭ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ው​ንም ውኃ የሚ​ነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች