ዘኍል 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በእሳት ከሚቀርበው ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ ቍርባናቸውም ሁሉ፥ የኀጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ከተቀደሰውም ሁሉ ለአንተ ለልጆችህም ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ለእኔ ከሚቀርብልኝ እጅግ ከተቀደሰው መባ ሁሉ፣ በእሳት የማይቃጠለው የራስህ ድርሻ ይሆናል፤ እጅግ የተቀደሰ አድርገው ከሚያመጡልኝ ስጦታ ከእህል ቍርባንም ሆነ ከኀጢአት ወይም ከበደል መሥዋዕት የሚነሣው ሁሉ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በእሳት ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ የእህሉ ቁርባናቸው ሁሉ፥ የኃጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ለአንተ ለልጆችህም እጅግ የተቀደሰ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ለእኔ ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ከእህል ቊርባን፥ ስለ ኃጢአት ስርየትና ስለ በደል ካሣ ከሚቀርበውም መባ ሁሉ፥ በእሳት የማይቃጠለው የመባ ድርሻ የአንተና የልጆችህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በእሳት ከሚቀርበው ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ የእህሉ ቍርባናቸው ሁሉ፥ የኃጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ለአንተ ለልጆችህም የተቀደሰ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |