Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 18:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እን​ዲሁ እና​ንተ ደግሞ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ዐሥ​ራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መባ ለይ​ታ​ችሁ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እናንተም ከእስራኤላውያን ላይ ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ፤ ከዚሁም የእግዚአብሔር ድርሻ የሆነውን ዐሥራት ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት አሥራት ሁሉ ለጌታ እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ ከእርሱም የጌታን የስጦታ ቁርባን ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚህ ዐይነት እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን ልዩ መባ ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር የምታመጡትን ይህን ልዩ መባ ለካህኑ አሮን ታስረክቡታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት አሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ የእግዚአብሔርንም የማንሣት ቍርባን ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 18:28
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ ሐዋ​ር​ያ​ችን ኢየ​ሱስ ከእኛ በፊት ወደ ገባ​ባት መጋ​ረ​ጃም ውስጥ የም​ታ​ስ​ገባ ናት።


የሳ​ሌም ንጉሥ መልከ ጼዴ​ቅም እን​ጀ​ራ​ንና የወ​ይን ጠጅን አወጣ፤ እር​ሱም የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን ነበረ።


መባ​ች​ሁም እንደ እህል ዐው​ድ​ማው ስን​ዴና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ይቈ​ጠ​ር​ላ​ች​ኋል።


ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተ​መ​ረ​ጠው ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ድርሻ ሁሉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የመ​ጀ​መ​ሪያ መባ ሁሉ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ከድ​ር​ሻ​ቸው እኩ​ሌታ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች