Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አንድ ወር የሆ​ነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅ​ደስ ሚዛን አም​ስት ሰቅል ነው። ይኸ​ውም ሃያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነዚህም አንድ ወር ሲሆናቸው ሃያ ጌራ በሚመዝነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ፣ በተወሰነው በመዋጃው ዋጋ በዐምስት ሰቅል ጥሬ ብር ትዋጀዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከአንድ ወር ጀምሮ የምትዋጀውን እንደ ግምትህ ትዋጀዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አንድ ወር የሞላቸው ሕፃናት በይፋ በተመደበው ዋጋ መሠረት አምስት ሰቅል ጥሬ ብር የቤዛ ዋጋ ተከፍሎላቸው ሊዋጁ ይችላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከአንድ ወር ጀምሮ የምትቤዠውን እንደ ግምትህ ትቤዠዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 18:16
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይቈ​ጠሩ ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፉት ሁሉ የሚ​ሰ​ጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ይሰ​ጣል። ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰ​ቅ​ሉም ግማሽ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ነው።


በየ​ራሱ አም​ስት ዲድ​ር​ክም ውሰድ፤ እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ብዛት ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ነው።


ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ይሁን፤ ሃያ ሰቅል፥ ሃያ አም​ስት ሰቅል፥ ዐሥራ አም​ስት ሰቅል፥ ምናን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ግም​ቱም ሁሉ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ይሆ​ናል፤ አንዱ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ይሆ​ናል።


የተ​ሰ​ጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድ​ን​ኳኑ ሥራ ሁሉ የተ​ደ​ረ​ገው ወርቅ፥ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክ​ሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።


በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ስለ ተረ​ፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥


ከሰው እስከ እን​ስሳ ቢሆን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ውን በኵ​ራት ፈጽሞ ትቤ​ዠ​ዋ​ለህ፤ ያል​ነ​ጹ​ት​ንም እን​ስ​ሳት በኵ​ራት ትቤ​ዣ​ለህ።


ነገር ግን የላ​ሞ​ቹን በኵ​ራት፥ ወይም የበ​ጎ​ቹን በኵ​ራት፥ የፍ​የ​ሎ​ች​ንም በኵ​ራት አት​ቤ​ዥም፤ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፤ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ ስባ​ቸ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች