Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆ​ነች የአ​ሮን በትር አቈ​ጠ​ቈ​ጠች፤ ለመ​ለ​መ​ችም፤ አበ​ባም አወ​ጣች፤ የበ​ሰለ ለው​ዝም አፈ​ራች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በማግስቱም ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ በሌዊ ቤት ስም የቀረበችው የአሮን በትር ማቈጥቈጥ ብቻ ሳይሆን እንቡጥ አውጥታ፣ አብባና አልሙን አፍርታ አገኛት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በማግስቱ ሙሴ ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ በሌዊ ነገድ ስም የቀረበችው የአሮን በትር ለምልማ አገኛት፤ ይኸውም እንቡጥ አውጥታ በማበብ የበሰለ የለውዝ ፍሬ አፍርታ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 17:8
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥ​ሙን ዛፍ ዝቅ ያደ​ረ​ግሁ፥ አጭ​ሩ​ንም ዛፍ ከፍ ያደ​ረ​ግሁ፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ያደ​ረ​ቅሁ፥ የደ​ረ​ቀ​ው​ንም ዛፍ ያለ​መ​ለ​ምሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ርሁ፤ እኔም አደ​ረ​ግሁ።”


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የመ​ረ​ጥ​ሁት ሰው በትር ትለ​መ​ል​ማ​ለች፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ባ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረም ከእኔ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።”


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል።


ከተ​መ​ረ​ጡት ጫፎ​ች​ዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬ​ዋ​ንም በላች፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም በትር ይሆን ዘንድ የበ​ረታ በትር የለ​ባ​ትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለል​ቅ​ሶም ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።


በሐ​ረ​ጉም ሦስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ወጡ፤ እር​ስ​ዋም ቅጠ​ልና አበባ አወ​ጣች፤ ዘለ​ላም አን​ጠ​ለ​ጠ​ለች፤ የዘ​ለ​ላ​ዋም ፍሬ በሰለ፤


በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


ነገር ግን በመ​ዓት ተነ​ቀ​ለች፤ ወደ መሬ​ትም ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልም ነፋስ ፍሬ​ዋን አደ​ረቀ፤ ብር​ቱ​ዎች በት​ሮ​ች​ዋም ተሰ​በ​ሩና ደረቁ፤ እሳ​ትም በላ​ቻ​ቸው።


በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥ እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ነው። ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥ ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።


ለቆ​ሬም ለማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ርሱ የሚ​ሆ​ኑ​ትን፥ ቅዱ​ሳ​ንም የሆ​ኑ​ትን ያያል፥ ያው​ቃ​ልም፤ የመ​ረ​ጣ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀ​ር​ባ​ቸ​ዋል።


ሙሴም በት​ሮ​ቹን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ አወ​ጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በት​ሩን ወሰደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች