Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 እነዚህም ሕይወታቸውን ለማጥፋት ኀጢአት የሠሩ ሰዎች ጥና ናቸው፤ ጥናዎቹም በእግዚአብሔር ፊት የቀረቡና የተቀደሱ በመሆናቸው ለመሠዊያው መለበጫ እንዲሆኑ ቀጥቅጠህ አሣሣቸው፤ እነዚህም ለእስራኤላውያን ማስጠንቀቂያ ይሁኑ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በኃጢአታቸው የተነሣ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለሞት የሰጡትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፋችሁ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጓቸው፤ በጌታ ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ጥናዎቹም የተቀደሱት ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ በቀረቡ ጊዜ ነው፤ ስለዚህ በኃጢአታቸው የተገደሉትን የእነዚህን ሰዎች ጥናዎች ውሰድና በመቀጥቀጥ እንዲሳሱ አድርግ፤ ለመሠዊያውም መክደኛ እንዲሆኑ አድርገህ ሥራቸው፤ ለእስራኤል ሕዝብ የመቀጣጫ ማስጠንቀቂያ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በኃጢአታቸው ሰውነታቸውን ያጠፉትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፈህ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጋቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:38
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥


ፊቴ​ንም በዚያ ሰው ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ጠ​ፋም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


የንጉሥ ቍጣ ከአንበሳ ቍጣ አያንስም፤ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።


ማኅ​በ​ሩም በሞቱ ጊዜ ምድ​ሪቱ አፍ​ዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠ​ቻ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ እሳ​ቲቱ ሁለት መቶ አም​ሳ​ውን ሰዎች አቃ​ጠ​ለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለም​ል​ክት ሆኑ።


ብዙ አሕዛብን አጥፍተሃልና ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን፦ እን​ዲህ ሲል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ። “አዶ​ን​ያስ ይህን ቃል በሕ​ይ​ወቱ ላይ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።”


እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።


በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።


መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው።


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጅ ለአ​ል​ዓ​ዛር እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፥ “ከተ​ቃ​ጠ​ሉት ሰዎች መካ​ከል የናስ የሚ​ሆኑ ጥና​ዎ​ችን አውጣ፤ ከሌላ ያመ​ጡ​ትን ያንም እሳት ወዲያ ጣል፤


የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር የተ​ቃ​ጠ​ሉት ሰዎች ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውን የናስ ጥና​ዎች ወስዶ ጠፍ​ጥ​ፎም ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በጫ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች