Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጅ ለአ​ል​ዓ​ዛር እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፥ “ከተ​ቃ​ጠ​ሉት ሰዎች መካ​ከል የናስ የሚ​ሆኑ ጥና​ዎ​ችን አውጣ፤ ከሌላ ያመ​ጡ​ትን ያንም እሳት ወዲያ ጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 “ጥናዎቹ የተቀደሱ ናቸውና ከተቃጠሉት ሰዎች ዘንድ ወስደህ በውስጣቸው ያለውን ፍም አርቆ እንዲደፋ ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር ንገረው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 “ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የተቀደሱ ናቸውና ጥናዎቹን ከሚነድደው እሳት መከካከል ውሰድ፥ እሳቱንም ወደ ውጭ አርቀህ በትነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 “የአሮን ልጅ አልዓዛር ከነሐስ የተሠሩትን ጥናዎች ከተቃጠሉት ሰዎች ዘንድ እንዲወስድና ጥናዎቹ የተቀደሱ ስለ ሆኑ በውስጣቸው ያለውን ፍም ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያፈስ ንገረው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ተቀድሰዋልና ጥናዎቹን ከተቃጠሉት ዘንድ ውሰድ፥ እሳቱንም ወደ ውጭ ጣለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:37
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጥና​ውን ወሰደ፤ እሳ​ትም አደ​ረ​ገ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨመ​ረ​በት፤ ሙሴና አሮ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ቆሙ።


ነገም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እሳት አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ዕጣ​ንም ጨም​ሩ​ባ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​መ​ር​ጠው ይህ ሰው ለሌዊ ልጆች ቅዱስ ይሁ​ን​ላ​ቸው።”


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እን​ስሳ ወይም የር​ስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይ​ሸ​ጥም፤ አይ​ቤ​ዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው።


የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች