Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 15:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም የኢን መስ​ፈ​ሪያ የሆነ መል​ካም ዱቄት አራ​ተኛ እጅ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ወይም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድ​ርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለሚቃጠል ወይም ለዕርድ መሥዋዕት ከሚቀርብ ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋራ የሂን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ የመጠጥ ቍርባን ዐብራችሁ አዘጋጁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ከሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ከሌላ መሥዋዕት ጋር ለእያንዳንዱ ጠቦት ታዘጋጃለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንዲሁም ለያንዳንዱ ጠቦት ለመጠጥ ቊርባን የሚሆን ሩብ ሊትር የወይን ጠጅ ከሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት ጋር ታቀርባላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 15:5
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ስብና ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ቀ​ር​በው የመ​ጠጥ ቍር​ባን ጋር ብዙ ነበረ። እን​ዲ​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ተዘ​ጋጀ።


ስለ​ዚህ በዚህ መጽ​ሐፍ ያዘ​ዝ​ሁህ ትእ​ዛዝ ይህ ነው። በዚህ ገን​ዘብ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና አውራ በጎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም፥ የእ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንና የመ​ጠ​ጣ​ቸ​ውን ቍር​ባን ተግ​ተህ ግዛ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ር​ባ​ቸው።


ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


“ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መባ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ቢሆን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን፥ የፊት እግ​ሮ​ቹ​ንና ራሱን ጨምሮ ያቀ​ር​በ​ዋል።


የስ​ን​ዴም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ይሁን፤ የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን የወ​ይን ጠጅ የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ ይሁን።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባኑ ከበ​ጎች ተባት ወይም እን​ስት ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ያቀ​ር​ባል።


ለቍ​ር​ባኑ የበግ ጠቦ​ትን ቢያ​ቀ​ርብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤


በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።


“እን​ዲሁ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ወይ​ፈን፥ ወይም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አውራ በግ፥ ወይም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ተባት የበግ ወይም የፍ​የል ጠቦት ይደ​ረ​ጋል።


ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።


የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ለአ​ንድ ጠቦት የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተ​ኛው እጅ ነው፤ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መጠጥ ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ።


ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤


በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል።


ወይ​ኑም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሰውን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን የወ​ይን ጠጅ​ነ​ቴን ትቼ በዛ​ፎች ላይ እነ​ግሥ ዘንድ ልሂ​ድን? አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች