ዘኍል 15:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ያለ ዕውቀት ተደርጎአልና ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወደ እናንተም ለሚመጣ መጻተኛ ስርየት ይደረግላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ባለማወቅ የተደረገውን ስሕተት ሁሉም የፈጸሙት ስለ ሆነ፣ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብና በመካከላቸው የሚኖር መጻተኛ ሁሉ ይቅር ይባላል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፥ ሕዝቡም ሁሉ ባለማወቅ ይህ ስሕተት ፈጽመዋልና በመካከላቸውም ለሚኖሩት መጻተኞች ስርየት ይደረግላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ሁሉም በአንድነት የስሕተቱ ተካፋዮች ስለ ሆኑ መላው የእስራኤል ማኅበርና በእነርሱም መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ያለ እውቀት ተደርጎአልና ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በመካከላቸውም ለሚኖሩት መጻተኞች ስርየት ይደረግላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከት |