Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በእ​ው​ነት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር አያ​ዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለይ​ተው ለማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸው፥ የሚ​ያ​ው​ቀው ለሌለ ለታ​ናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለጥ​ፋት ያነ​ሳ​ሱኝ ሁሉ አያ​ዩ​አ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ለአባቶቻቸው እሰጣቸው ዘንድ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም። የናቀኝ ማንኛውም ሰው ፈጽሞ አያያትም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፥ እነዚህም የናቁኝ ሰዎች ሁሉ አያይዋትም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር በፍጹም አይገቡም፤ እኔን ከናቁኝ ሰዎች መካከል አንድ እንኳ ወደዚያች ምድር ከቶ አይገባም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 14:23
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከግ​ብፅ የወ​ጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ውቁ ሰዎች እኔን ፈጽ​መው አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​ምና ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰጥ ዘንድ የማ​ል​ሁ​ባ​ትን ምድር አያ​ዩም፤


ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚያ መካ​ከል አን​ድም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ታ​ምር ወደ ሰጠ​ኋ​ቸው ምድር እን​ዳ​ላ​ገ​ባ​ቸው በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነ​ሣሁ።


ሥራዉ ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈ​ጸም፥ “እን​ግ​ዲህ ወደ ዕረ​ፍቴ አይ​ገ​ቡም ብዬ በቍ​ጣዬ ማልሁ” እን​ዳለ እኛስ ያመ​ንን ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ገ​ባ​ለን።


ወደ ሰማይ ይወ​ጣሉ፥ ወደ ጥል​ቅም ይወ​ር​ዳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በመ​ከራ ቀለ​ጠች።


ሰማ​ያት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ባሕር ሞላዋ ትና​ወ​ጣ​ለች፤


ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።


እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ግቡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ውረሱ።


በፊቴ ክፉን ነገር ቢያ​ደ​ርጉ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ስለ ተና​ገ​ር​ሁት መል​ካም ነገር እጸ​ጸ​ታ​ለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች