Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ወደ ወይን ዘለላ ሸለ​ቆም መጡ፤ አዩ​ኣ​ትም፤ ከዚ​ያም ከወ​ይኑ አንድ ዘለላ የነ​በ​ረ​በ​ትን አረግ ቈረጡ፤ በመ​ሎ​ጊ​ያም ተሸ​ከ​ሙት፤ ደግ​ሞም ከሮ​ማኑ ከበ​ለ​ሱም አመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ይህንም ከሮማንና ከበለስ ጋራ በመሎጊያ አድርገው ለሁለት ተሸከሙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አልፈውም ወደ ኤሾኮል ሸለቆ ደረሱ፤ ከዚያም የወይን ዘለላ ያለበትን ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ያንንም የወይን ዘለላ አንድ ሰው ብቻውን ሊሸከመው የማይችል ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሁለት ሰዎች በመሎጊያ በትከሻቸው ላይ ተሸከሙት፤ ከዚህም ጋር የሮማንና የበለስ ፍሬ ይዘው መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ሁለቱም ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 13:23
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከዚያ ስለ ቈረ​ጡት ዘለላ የዚ​ያን ስፍራ ስም የወ​ይን ዘለላ ሸለቆ ብለው ጠሩት።


ከዚህ በኋላ በሶ​ሬሕ ሸለቆ የነ​በ​ረች ደሊላ የተ​ባ​ለች አን​ዲት ሴትን ወደደ።


ከአ​መ​ለ​ጡ​ትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕ​ብ​ራ​ዊው ለአ​ብ​ራ​ምም ነገ​ረው፤ እር​ሱም የኤ​ስ​ኮል ወን​ድ​ምና የአ​ው​ናን ወን​ድም በሆነ በአ​ሞ​ራ​ዊው የመ​ምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነ​ዚ​ያም ከአ​ብ​ራም ጋር ቃል ኪዳን ገብ​ተው ነበር።


ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች