Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሙሴም የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ይሰ​ልሉ ዘንድ ላካ​ቸው፤ አላ​ቸ​ውም፥ “ከዚህ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ፥ ወደ ተራ​ሮ​ችም ውጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ኔጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሙሴም የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ላካቸው፥ እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “ከዚህ በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ውጡ፥ ወደ ተራራማውም አገር ሂዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሙሴም ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ወደ ተራራማው አገር ውጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፥ አላቸውም፦ ከዚህ በደቡብ በኩል ውጡ፥ ወደ ተራሮችም ሂዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 13:17
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ያም በኋላ የይ​ሁዳ ልጆች በተ​ራ​ራ​ማው ሀገ​ርና በደ​ቡብ በኩል በቈ​ላው ውስጥ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ሊወጉ ወረዱ።


አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከይ​ሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁ​ዳም ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር ወረሰ፤ በሸ​ለ​ቆው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ግን የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሊወ​ር​ሳ​ቸው አል​ቻ​ለም።


ዓስ​ካም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና ውኃ የማ​ጣ​ቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለ​ችው። ካሌ​ብም በል​ብዋ እንደ ተመ​ኘ​ችው የመ​ከ​ራ​ዋ​ንና የኀ​ዘ​ኗን ዋጋ ሰጣት።


ከዚ​ያም በአ​ቅ​ረ​ቢን ዐቀ​በት ፊት ይሄ​ዳል፤ ወደ ጺንም ይወ​ጣል፤ በቃ​ዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወ​ጣል፤ በአ​ስ​ሮ​ንም በኩል ያል​ፋል፤ ወደ ሰራ​ዳም ይወ​ጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕ​ራ​ብም ይዞ​ራል።


አብ​ራ​ምም ከግ​ብፅ ወጣ፤ እር​ሱና ሚስቱ፥ ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ፥ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ።


በዚ​ያም ተራ​ራማ አገር ይኖሩ የነ​በሩ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ወጥ​ተው ተጋ​ጠ​ሙ​አ​ችሁ፤ ንብ እን​ደ​ም​ት​ነ​ድ​ፍም ነደ​ፉ​አ​ችሁ፤ አሳ​ደ​ዱ​አ​ች​ሁም፤ ከሴ​ይር እስከ ሔር​ማም ድረስ መቱ​አ​ችሁ።


በነ​ጋ​ውም ማል​ደው ተነሡ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ራስ ወጥ​ተው፥ “እነሆ፥ እኛ ከዚህ አለን፤ በድ​ለ​ና​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ስፍራ እን​ወ​ጣ​ለን” አሉ።


ደግ​ሞም በዚያ የዔ​ና​ቅን ዘሮች አየን፤ በአ​ዜብ በኩል ዐማ​ሌቅ ተቀ​ም​ጦ​አል፤ በተ​ራ​ሮ​ች​ዋም ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውና ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውም ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውም በባ​ሕር ዳርና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ወንዝ አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጦ​አል።”


ያም የጨው ሸለቆ የዝ​ፍት ጕድ​ጓ​ዶች ነበ​ሩ​በት። የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉ​ሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀ​ሩ​ትም ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ሸሹ።


ከአ​ዜብ ባደ​ረ​ገው በጕ​ዞ​ውም ወደ ቤቴል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስ​ቀ​ድሞ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል ድን​ኳን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረው ነው፤


ተነሣ፤ በም​ድር በር​ዝ​መ​ቷም፥ በስ​ፋ​ቷም ዙር፤ እር​ስ​ዋን ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።”


ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዴት እንደ ሆነች፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሰዎች ብር​ቱ​ዎች ወይም ደካ​ሞች፥ ጥቂ​ቶች ወይም ብዙ​ዎች እንደ ሆኑ፥


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ።


እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች