Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 11:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የበ​ሬና የበግ መንጋ ቢታ​ረድ፥ የባ​ሕር ዓሣ ሁሉ ቢሰ​በ​ሰብ ይበ​ቃ​ቸ​ዋ​ልን?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ታዲያ ስንት የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋ ቢታረድላቸው ይበቃ ይሆን? በባሕር ያለው ዓሣ ሁሉ ቢያዝ ሊዳረሳቸው ይችላልን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እነርሱን የሚያጠግብ የበሬና የበግ መንጋ ይታረድላቸውን? ወይስ የባሕርን ዓሣ ሁሉ እንዲያጠግባቸው ይሰበሰብላቸውን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ታዲያ ምን ያኽል የከብትና የበግ መንጋ ቢታረድ እነርሱን ሊያጠግብ ይችላል? በባሕር ውስጥ ያለው ዓሣ ሁሉ ቢሰበሰብ ለእነርሱ በቂ ሊሆን ይችላልን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እነርሱን የሚያጠግብ የበሬና የበግ መንጋ ይታረድን? ወይስ የባሕርን ዓሣ ሁሉ ያጠግባቸው ዘንድ ይሰበሰብላቸዋልን? አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 11:22
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደቀ መዛሙርቱም “ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?” አሉት።


ንጉ​ሡም በእጁ ተደ​ግ​ፎት የሚ​ቆም የነ​በረ ያ ብላ​ቴና ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ደ​ርግ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፤ ከዚያ ግን አት​ቀ​ም​ስም” አለ።


“አም​ስት የገ​ብስ እን​ጀ​ራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላ​ቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነ​ዚህ ይህን ለሚ​ያ​ህል ሰው ምን ይበ​ቃሉ?”


ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “ወንድ ስለ​ማ​ላ​ውቅ ይህ እን​ዴት ይሆ​ን​ል​ኛል?” አለ​ችው።


ዘካ​ር​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዲህ አለው፥ “ይህ እን​ደ​ሚ​ሆን በምን አው​ቃ​ለሁ? እነሆ፥ እኔ አር​ጅ​ች​አ​ለሁ፤ የሚ​ስ​ቴም ዘመ​ንዋ አል​ፏል።”


ደቀ መዛሙርቱም “በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል?” ብለው መለሱለት።


እርሱ ግን መልሶ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። “ሄደን እንጀራ በሁለት መቶ ዲናር እንግዛላቸውን? እንዲበሉም እንስጣቸውን?” አሉት።


በፊቴ ያለ​ቅ​ሳ​ሉና፦ የም​ን​በ​ላ​ውን ሥጋ ስጠን ይላ​ሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የም​ሰ​ጠው ሥጋ ከየት አለኝ?


ሙሴም፥ “እኔ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያለሁ ሕዝብ ስድ​ስት መቶ ሺህ እግ​ረኛ ናቸው፤ አን​ተም፦ ሥጋን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ወር ሙሉም ይበ​ሉ​ታል አልህ።


እግ​ዚ​አ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አት​ች​ል​ምን? አሁን ቃሌ ይፈ​ጸም ወይም አይ​ፈ​ጸም እንደ ሆነ እነሆ፥ አንተ ታያ​ለህ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች