Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ላይ ክፉ አደ​ረ​ግህ? ለም​ንስ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አላ​ገ​ኘ​ሁም? ለም​ንስ የዚ​ህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደ​ረ​ግህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እርሱም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “እንዲህ ያለውን መከራ በባሪያህ ላይ ለምን አመጣህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም የጫንህብኝስ ምን አስቀይሜህ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሙሴም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለምን በባርያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ “ይህን ከባድ ነገር በእኔ በአገልጋይህ ላይ ስለምን አመጣህብኝ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? የዚህን ሁሉ ሕዝብስ ከባድ ኀላፊነት ለምን በእኔ ላይ ጫንከው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 11:11
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ ብቻ​ዬን ድካ​ማ​ች​ሁን፥ ሸክ​ማ​ች​ሁ​ንም፥ ክር​ክ​ራ​ች​ሁ​ንም እሸ​ከም ዘንድ እን​ዴት እች​ላ​ለሁ?


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለ​ሰና፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ​ምን ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፋህ? ስለ ምንስ ላክ​ኸኝ?


የቀ​ረ​ው​ንም ነገር ሳል​ቈ​ጥር ዕለት ዕለት የሚ​ከ​ብ​ድ​ብኝ የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ አሳብ ነው።


እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?


የሚ​ያ​ሳ​ዝ​ኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበ​ረ​ታሉ? ቍስ​ሌስ ስለ ምን የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆነ? ስለ ምንስ አል​ሽ​ርም አለ? እንደ ሐሰ​ተኛ ምንጭ፥ እን​ዳ​ል​ታ​መ​ነች ውኃም ሆነ​ብኝ።


እናቴ ሆይ! ለም​ድር ሁሉ የክ​ር​ክ​ርና የጥል ሰው የሆ​ን​ሁ​ትን እኔን ወል​ደ​ሽ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! ለማ​ንም አል​ጠ​ቀ​ም​ሁም፤ ማንም እኔን አል​ጠ​ቀ​መ​ኝም፤ ከሚ​ረ​ግ​ሙ​ኝም የተ​ነሣ ኀይሌ አለቀ።


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እስ​ራ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይታ​መ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦ ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤ ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?


እን​ዲ​ህስ ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ፥ በፊ​ትህ ይቅ​ር​ታን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ፥ እባ​ክህ፥ ፈጽሞ ግደ​ለኝ።”


ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።”


ሙሴም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ፥ ሲያ​ለ​ቅሱ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ተቈጣ፤ ነገ​ሩም በሙሴ ፊት ክፉ ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች