Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከእ​ር​ሱም በኋላ ሌዋ​ው​ያ​ንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቅ​ዒላ ግዛት እኩ​ሌ​ታና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ገዢ አሰ​ብያ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከርሱ ቀጥሎ ሌዋውያኑ በባኒ ልጅ በሬሁ ሥር ሆነው የዕድሳት ሥራ ሠሩ። ከርሱ ቀጥሎ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ ሐሸብያ አውራጃውን መልሶ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሑም አደሱ። በአጠገቡ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዢ ሐሻብያ ስለ አውራጃው ብሎ አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሁም አደሱ። በአጠገባቸውም የቅዒላ ግዛት እኩሌታ አለቃ ሐሸብያ ስለ ግዛቱ አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።


ሴኬ​ንያ፥ ሬሁም፥ ሜራ​ሞት፤


ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤ​ሶር ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የዓ​ዛ​ቡህ ልጅ ነህ​ምያ በዳ​ዊት መቃ​ብር አን​ጻር እስ​ካ​ለው ስፍራ፥ እስከ ተሠ​ራ​ውም መዋኛ፥ እስከ ኀያ​ላ​ኑም ቤት ድረስ ሠራ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የቅ​ዔላ ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የኤ​ን​ሐ​ዳድ ልጅ ቤኒ​ይና ወን​ድ​ሞቹ ሠሩ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች፥ የሰ​ራ​ብያ ልጅ ሴኬ​ንያ፥ የከ​ናኒ ልጆ​ችም በደ​ረ​ጃ​ዎች ላይ ቆመው ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላቅ ድምፅ ጮኹ።


ኤላም፥ አቁ​ዛም፥ ኬዜብ ቴርሳ፥ ኤሎ​ምም፥ ዐሥር ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች